የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ ዳቪድ ራያ የተሻሻለ ውል ቀረበለት

You are currently viewing የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ ዳቪድ ራያ የተሻሻለ ውል ቀረበለት

AMN-መስከረም 27/2018 ዓ.ም

በአርሰናል ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው ዳቪድ ራያ ደሞዙን የሚያሻሽልለት ውል ቀርቦለታል፡፡

ስፔናዊ ግብጠባቂ እስከ 2028 የሚቆየው ውል እንደተጠበቀ ሆኖ ደሞዙ ግን እንደሚጨምርለት ቢ ቢ ሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡

ራያ በ2023 ነበር ከብሬንትፎርድ አርሰናልን የተቀላቀለው፡፡ የ30 ዓመቱ ግብ ጠባቂ በአርሰናል የሚያገኘው ደሞዝ በሳምንት 100 ሺ ፓውንድ እንደሆነ ዘገባው አስታውሷል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review