የ7ኛው የታማኝ ግብር ከፋይ እውቅና ሥነሥርዓት ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ባለፈው ዓመት የምታዋጡት ግብር ለጋራ እድገት እና ለሕዝባዊ ጠቀሜታ በሚውሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚውል ቃል ገብተን ነበር።

ዛሬ በከተማችን ኮሪደሮች የሚታየው ለውጥ ለዚያ ቃላችን ሕያው ምስክር ሆኖ ይታያል። አስታውሱ፣ የዛሬ ጥረታችሁ የነገን ትውልድ የተሻለ መፃኢ እድል እየቀረፀ ነው ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልፀዋል።
ሙስናን እና ሌብነትን ለማስወገድ በምናደርገው ጥረት ሥርዓቶቻችንን ማጠናከራችንን እንቀጥላለን። ግብር ከፋዮችም በመሰል ጎጂ ተግባር የተሠማሩ ሰዎችን ባለመተባበር እንዲያግዙ አሳስባለሁ። በጋራ ግልጽ፣ ተጠያቂነት የሰፈነባት እና የበለጸገች ሀገር እንገነባለንም ብለዋል።