ያለምንም ገንዘብ ዕርዳታም ሆነ ብድር በታማኝ ግብር ከፋዮቻችን ብር ብቻ ሀገር እየተሠራች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት 7ኛው የታማኝ ግብር ከፋይ ዕውቅና እና ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።
በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር፤ ታማኝ ግብር ከፋዮችን ማመስገን እና ደስታቸውን መጋራት መበልጸግ ለሚፈልግ ሀገር በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በብድርም ሆነ በዕርዳታ አንድ ዶላርም ሆነ አንድ ብር ሳይታከልበት በግብር ከፋዮች ገንዘብ ያ የቆሸሸ ከተማችንን ለልጆቻችን በሚመጥን መልክ እየሠራን ነው ብለዋል በንግግራቸው።
ለዚህም አዲስ አበባን ተዘዋውሮ መጎብኘት ጥሩ ማሳያ መሆኑን ነው ያስረዱት።
በመሆኑም በእናንተ ታማኝ ግብር ከፋዮች ገንዘብ ሀገር እየተሠራች መሆኑን ዳግም በኩራት ልገልጽላችሁ እወዳለሁ ሲሉም ገልጸዋል።