ኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ሀይል ለጎረቤት ሀገራት በማቅረብ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ መሆኗ ተገለፀ

You are currently viewing ኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ሀይል ለጎረቤት ሀገራት በማቅረብ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ መሆኗ ተገለፀ

AMN – መስከረም 28/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ለውጭ ሀገራት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል በማቅረብ ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ እንደሆነች አፍሪካን ኒውስ ኤጄንሲ ዘግቧል።

በተያዘው የፈረንጆቹ አመት የመጀመሪያ 6ወራት ኢትዮጵያ 1200 ጊጋዋት ሰአት ኤሌክትሪክ ሀይል ለኬንያ ማቅረቧን ዘገባው ጠቅሷል።

የሀገሪቱን የኢነርጂና ነዳጅ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ጠቅሶ እንደዘገበው ኬንያ እስከ ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ድረስ ከውጭ ካስገባችው ጠቅላላ የኤሌክትሪክ ኃይል 83 በመቶው ከኢትዮጵያ የተገኘ ነው፡፡

በዚህም ኬንያ በዓመት 10 ሚሊየን ዶላር ገደማ ማዳን መቻሏን ዘገባው አክሏል።

የኬንያ አጠቃላይ የኤሌትሪክ ኃይል አቅርቦት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ27.8 በመቶ ከፍ ብሏል፤ ይህም ኬኒያ ከኢትዮጵያ ጋር የፈጸመችውን የኃይል አቅርቦት ስምምነት ተከትሎ የተመዘገበ መሆኑ ተገልጿል።

እ.ኤ.አ. በ2025 አጋማሽ ላይ ኬንያ 751.95 ጊጋዋት ሰአት ከኢትዮጵያ የገዛች ሲሆን ይህ በ2024 በተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው 419.13 ጊጋዋት ሰአት፤ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ የታየበት ነው።

ኬኒያ እየጨመረ የመጣውን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ለማሟላት እና የፈረቃ አገልግሎትን ለማስቀረት በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ የምታገኘውን አቅርቦት ከ50-100 ሜጋ ዋት ለማሳደግ ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል ።

በዳዊት በሪሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review