ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከጳጉሜን ወር 2017 ጀምሮ በተከበሩት የአደባባይ በዓላት እና ከተማዋ ላስተናገደቻቸው ትላልቅ አህጉር ዓቀፍ እና አለም አቀፍ መድረኮች ስኬት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በሂደቱ ተሳታፊ ለነበሩ ባለድርሻ አካላት የምስጋና ፕሮግራም ተካሄዷል፡፡
በቅርቡ የተከበረው የመስቀል ደመራ እና የሆረ ፊንፊኔ እንዲሁም ሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓላት እጅግ በደመቀ እና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ መከበሩንም ገልፀዋል።
ከንቲባ አዳነች አክለውም፣ የበዓላቱ አከባበር የህዝቡን ማህበራዊ መስተጋብር ጥንካሬ እና አንድነቱን በጉልህ ያሳየ ነበር ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ ያስተናገገደችው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ፣ የወንጌላዊያን አማኞች የምስጋና መርሃ ግብር፣ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የደስታ የድጋፍ ሰልፍ እና ሌሎችም መድረኮች በስኬት መጠናቀቅ የህዝቡን ጨዋነት እና የእንግዳ ተቀባይነት የሚያሳይ ነው ብለዋል ከንቲባዋ።
በአፈወርቅ አለሙ