በካይ የፍሳሽ ቆሻሻን ወደ ወንዝ የለቀቀ የንግድ ተቋም 300 ሺህ ብር መቀጣቱን ባለስልጣኑ አስታወቀ

You are currently viewing በካይ የፍሳሽ ቆሻሻን ወደ ወንዝ የለቀቀ የንግድ ተቋም 300 ሺህ ብር መቀጣቱን ባለስልጣኑ አስታወቀ

AMN መስከረም 28/2018

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እየተሰራ ባለው የአፍንጮ በር የወንዝ ዳርቻ ልማት ላይ በካይ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቀ የንግድ ተቋም (ጠጅ ቤት) 300 መቶ ሺ ብር መቅጣቱን የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ።

ድርጅቱ በተደጋጋሚ ወደ ወንዝ የሚለቀውን በካይ የፍሳሽ ቆሻሻ እንዲያቆም ግንዛቤ ቢፈጠርለትም ከድርጊቱ መቆጠብ ባለመቻሉ እርምጃ መዉሰዱን ባለስልጣኑ ገልጿዋል።

መሰል ደንብ መተላለፎች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ የገለጸዉ ባለስልጣኑ ደንብ ተላላፊዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review