ኢትዮጵያ ሁለተኛ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ድሏን አሳካች

You are currently viewing ኢትዮጵያ ሁለተኛ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ድሏን አሳካች

AMN-መስከረም 28/2018 ዓ.ም

በሩዋንዳ አማሆሮ ስታዲየም ጊኒ ቢሳውን የገጠመችው ኢትዮጵያ 1ለ0 አሸንፋለች።

የዋልያዎቹን የድል ግብ ተከላካዩ ራምኬል ጀምስ ከመረብ አሳርፏል።

በምድብ አንድ የምትገኘው ኢትዮጵያ ድሉን ተከትሎ ነጥቧን ዘጠኝ አድርሳለች።

ለዓለም ዋንጫ እንደማታልፍ ቀድማ ያወቀችው ኢትዮጵያ ዛሬ ያሳካችው ድል ሁለተኛዋ ሆኖ ተመዝግቧል።

የመጀመሪያ ድሏን ጅቡቲ ላይ ማግኘቷ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ ሰኞ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታዋን ከ ቡርኪና ፋሶ ጋር ታደርጋለች።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review