ኢትዮጵያ ህጋዊ በሆነ መንገድ ቀይ ባህርን መጠቀም እንደምትችል የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ተናገሩ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ህጋዊ በሆነ መንገድ ቀይ ባህርን መጠቀም እንደምትችል የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ተናገሩ

AMN-መስከረም 29/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ህጋዊ በሆነ መንገድ መጠቀም እንደምትችል የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ከአል አረቢያ የዜና ጣብያ የእንግሊዝኛው ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ቀይ ባህር ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጥቅም ያለው ስፍራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እንደ ስጋት መታየት ያለበት ጉዳይ አለመሆኑን አንስተው፤ ጥያቄው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸውን መመዘኛዎች በመከተል መፍትሄ እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ ነው ያሉት ።

በአህጉሩ ውስጥ 16 የአፍሪካ ሀገራት የባህር በር የሌላቸው እንደሆኑ የጠቀሱት ሀሰን ሼክ ቀይ ባህር አፍሪካን ከበው ከሚገኙት ባህሮች መካከል አንዱ ነው ብለዋል።

አክለውም “ኢትዮጵያ ቀይ ባህር ለመጠቀም ተገቢ መንገዶችን እስከተከተለች ድረስ የመጠቀም መብት አላት ብየ አምናለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

ቀይ ባህር በጣም አስፈላጊ እና ስትራቴጂካዊ ባህር መሆኑን ተከትሎ ፤በቀይ ባህር ድንበር ያላቸው እና ስለ ቀይ ባህር ደህንነት ስጋት ያላቸው ሁሉም ሀገራት መስማማት እና እርስ በርስ መግባባት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ሶማሊያ ሉአላዊነትን ያከበረ ማንኛውም የተጠቃሚነት ጥያቄ እንደምታከብር የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ በቃለ መጠይቁ ላይ አመላክተዋል ።

በዳዊት በሪሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review