የምክር ቤት አባላት በሀሳብና በተግባር ወደ ህዝቡ በመቅረብ በህዝብና መንግስት መካከል መዳላድልን ለመፍጠር እያደረጉት ያለውን ጥረት አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዋና አፈ -ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ገለፁ::
የካ ክፍለ ከተማን በመወከል የአዲስ አበባ ምክር አባላት የሆኑ ተመራጮች ከመረጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ ።
የምክር ቤቱ አባላት ከመረጣቸው ህዝብ ጋር ውይይት ማድረጋቸው አንዱ የዲሞክራሲ ስርአት ማሳያ ነው ያሉት የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ይህም የህዝብን ጥያቄ ለመመለስና ዘላቂ መፍትሄን ለመስጠት የሚያስችል ቁልፍ መሳሪያ ነው ብለዋል።

የምክር ቤቱ አባላት ወደ ህዝቡ በመቅረብ የሚያደረጓቸው ውይይቶች የህዝብ ጥያቄዎች እንዲፈቱ በማስቻል ረገድ ትልቅ ሚና እንዳላቸው አንስተዋል ፡፡
ምክር ቤቶች የህዝብ ሉአላዊነት መገለጫ ተቋማት እንደመሆናቸው መጠን የህዝብ የልብ ትርታ ቀርበው በማድመጥ በርካታ የህዝብ ችግሮችንም መፍታት መቻሉም ተጠቁማል።
በውይይቱ ባለፈው በጀት አመት የተከናወኑ ተግባራትና የቀጣይ የቤት ስራዎችን የተመለከተ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
በራሔል አበበ