የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ነዉ

You are currently viewing የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ነዉ

‎AMN መስከረም 29/2018ዓ.ም

‎የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ይገኛል።

‎በመደበኛ ጉዔው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማን ጨምሮ ፣ የጉባኤው የቦርድ አመራሮች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተገኝተዋል።

‎ጉባኤውን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሃፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ እንደተናገሩት ፣ የ2017 የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 የዕቅድ ሪፖርት ላይ የጉባኤዉ ትኩረት መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም በሀይማኖቶች መካከል ልዩነት ለመፍጠር የሚተጉ አካላትን መታገል እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በዘርፉ ያለውን ችግር ለመከላከል መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት እናደንቃለን ያሉት ዋና ፀሀፊው፣ከዚህ በላይ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም ገልጸዋል።

‎የአዲስ አበባ፣ሀዲያ እና ስልጤ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የአዲስ አበባ ከተማ የሀይማኖት ጉባኤ ቦርድ ሰብሳቢ አባ ህርያቆስ በበኩላቸው፣ ሀይማኖቶች በስነምግባር ህግ አንድ በመሆናቸውን ፣ ስለዚህ ሀይማኖትን ከምግባር ጋር አጣምሮ መኖር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

‎”ፈጣሪ የሚያዘውን መልካም ስራ ልንሰራ እንደሚገባ የጠቆሙት አባ ህርያቆስ፣በያለንበት እምነት ለሰዎች ሁሉ በጎ ስራን ልንሰራ ያስፈልጋል ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል ።

‎የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን እንዳስረዱት፣” ስንተባበር ለሁላችንም የምትመች ሀገር” መገንባት እንደሚቻል ገልጸዋል።

‎የዕምነት ብዝሃነት የመለያየት ሳይሆን አብሮ የማደግ ማሳያ ናቸው ያሉት ሼህ ኤባ ደግሞ አዲስ አበባ የአብሮነት መገለጫ እንድትሆን የሀይማኖት ተቋማት በአንድነት ሲቆሙ የኢትዮጵያ ልማት እውን ይሆናል ብለዋል።

‎የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣መንግስት በሰራው ስራ የአደባባይ በአላት በሰላም ማለፉን፣በዚህ ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ድርሻ ጉልህ መሆኑን ተናግረዋል።

‎በሀይማኖቶች መካከል መለያየትን የሚፈጥሩ አካላትን ለመከላከል መስራት ይገባል፣እነዚህን አካላት ለህግ የማቅረብ ስራ ይሰራልም ብለዋል።

‎የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ከተማዋን የሚመጥን ሰላም እና ደህንነት ለማምጣት የሀይማኖት ተቋማት ኃላፊነት የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

‎ተቋማቱ በበርካታ የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያበረከቱት እና እያበረከቱት ያለው አስተዋፅዖ ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል።

‎የሀይማኖት ተቋማት ለተቋቋሙለት አላማ ብቻ እንዲውሉ ከሃይማኖት አባቶች ትልቅ ስራ እንደሚጠበቅም አጽንዖት ሰጥተዋል።

‎በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review