ጉለሌን ወክለው ለአዲስ አበባ ምክር ቤት የተመረጡ የምክር ቤት አባላት ከክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሾ ኦላና ህዝቡ ለሚያነሳው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እየተሰጡ ነው ብለዋል።
የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የከተማዋን እድገት የሚያሻሽሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የተናገሩት አቶ ማሾ ከዚህ የበለጠ ህዝቡ ተጠቃሚ እንዲሆን ምክር ቤቱ አስፈጻሚውን አካል የመከታተልና የመቆጣጠር ስራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

የጉለሌ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ መኩሪያ ጉርሙ በበኩላቸው ምክር ቤቱ ህዝቡ ለሚያነሳው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ፈጣን ምላሽ እንዲያገኝ ድልድይ ሆኖ እያገለገለ ነው ብለዋል።
በመራጭ ተመራጭ መድረኩ በቀጣይ ትኩረት ይሻሉ የተባሉ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያም ተሰጥቶባቸዋል።
በፍቃዱ መለሰ