በ19ነኛው የአዲስ አበባ ከተማ ህዳሴ ዋንጫ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ ለፍፃሜ ደርሷል።
ከአምስት ዓመት በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሸገር ደርቢ በጊዮርጊስ 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል።
በበርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ በተከናወነው ጨዋታ ቢንያም ፍቅሬ ሁለት እንዲሁም ፉአድ ኢብራሂም በራሱ ላይ ያስቆጠሯቸው ሦስት ግቦች ጊዮርጊስን ባለድል አድርገዋል።
በጨዋታው 2ለ0 መምራት ችሎ ለነበረው ኢትዮጵያ ቡና አቡበከር አዳሙ እና በፍቃዱ አለማየሁ ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል።
የፊታችን እሁድ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቻል ለፍፃሜ ሲጫወቱ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ለደረጃ ይጫወታሉ።
በሸዋንግዛው ግርማ