የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና የንግድ ስምምነት ትግበራን ለሀገራዊ ብልጽግና ለማዋል እንሰራለን ሲሉ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለፁ

You are currently viewing የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና የንግድ ስምምነት ትግበራን ለሀገራዊ ብልጽግና ለማዋል እንሰራለን ሲሉ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለፁ

AMN – መስከረም 29/2018 ዓ.ም

የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና የንግድ ስምምነት ትግበራን ለሀገራዊ ብልጽግና ለማዋል እንሰራለን ሲሉ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶር ) ገልጸዋል ።

የንግድ ስምምነት ግብይት ትግበራ እና ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት መሰረት ዛሬ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓም የተለያዩ ምርቶችን ለተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በመላክ የንግድ ትግበራን መጀመሯን ተከትሎ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።

የገቢና የወጭ ንግድ ስርዓትን ዘመናዊ እና የተሳለጠ የገበያ ስርዓትን መፍጠር የሚያስችል ቀጣናዊ ስምምነት መሆኑንም ገልጸዋል ።

ካሳሁን ጎፌ ( ዶ/ር ) ይህ የንግድ ትግበራ አዲስ የንግድ እና የግብይት ስርዓት ከመፍጠር ባለፈ የአፍሪካውያን ሀገራት ወንድማማችነት የሚያጎለብት ነው ብለዋል ።

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ዋና ጸሐፊ ተወካይ ሩይ ፔድሮ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ዕቅድን አፍሪካ የተሳሰረች ፣ የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን ግብ ለማሳካት እንደሚረዳ ገልጸዋል ።

የስምምነት ትግበራው ለኢትዮጵያውያን በንግድ እና ግብይት ዘርፍ አዲስ እና ሰፊ ዕድል ይዞ እንደሚመጣም ተወካዩ ገልጸዋል ።

እ.ኤ.አ በ2025 በጀት ዓመት አጋማሽ ድረስ ከ55 የአፍሪካ ሕብረት ሀገራት ከኤርትራ በስተቀር 54ቱ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነትን ተፈራርመዋል ተብሏል ።

ከመስራች ሀገራት ውስጥ ከ47 በላይ ሀገራት በሀገር ውስጥ ህጋቸው ስምምነቱን ማጽደቃቸው ተነግሯል ።

የፓናል ውይይቱ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች እና እንግዶች ተገኝተዋል ።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review