ዱቡሻና የዱቡሻ ወጋ ስርዓትን በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚረዳ የምክክር መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የውይይቱ ዋና አላማ ዱቡሻና የዱቡሻ ወጋ ስርዓትን በሰው ልጅ ወካይ ቅርስነት በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ለመገምገም እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
የክልሉ መንግስት የሀገር በቀል እሴቶችን ጠብቆ ለማቆየት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲያገኙ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡
በመድረኩ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የኢፌድሪ የቅርስና ጥናት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያለው እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የፕሬስ ሴክሬታሪያት ሀላፊ ኤደን ንጉሴ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ተናግረዋል፡፡