በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ያለዉን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ጎረቤት ሃገራትም እየተጋሩት ይገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ ጎረቤት ሃገር የሆነችዉ ኬኒያ እስከ 2032 ድረስ 15 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ሃገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ንቅናቄ ጀምራለች፡፡
የኬኒያዉ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በሃገር አቀፍ ደረጃ የተያዘዉን እቅድ ለማሳካት በመላ ሃገሪቱ ችግኝ እንደሚዘጋጅ ገልጸዋል፡፡
የሚተከሉት ችግኞችም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያግዙና የፍራፍሬ የወጪ ንግድን የሚያሳድጉ እንደሚሆኑም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ጠቅሰዋል፡፡
ከህጻናት ጀምሮ ሁሉም የሃገሪቱ ዜጎች በህብረት ችግኝ እንዲተክሉም ጠይቀዋል፡፡