በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን ስለ አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ እና አከፋፈል ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል ፡፡
ሀላፊው በ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ ከኢኮኖሚ እንቅስቃሴውና ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ በፌደራል መንግስት ለአጠቃላይ የመንግስት ሰራተኛ የደሞዝ ማሻሻያ ታወጆ ከመስከረም ጀምሮ ተግባዊ እንዲደረግም አቅጣጫ መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡
ለዚህም የከተማ አስተዳደሩን ዝግጅት በተመለከተ የሚመጣው የደሞዝ ልዩነቱ እንዴት ይሸፈናል ሚለውን አብራርተዋል ፡፡
በማብራሪያዉም የፌደራል መንግስት የአከፋፈል መመሪያውን ለማስፈፀም 7.7 ቢሊየን ብር ጭማሪ ጥሬ ገንዘብ ፈሰስ ማድረጉን ተከትሎ ቢሮው ጭማሪውን ለመክፈል የሚስችል ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታዉቀዋል፡፡
አቶ አብዱልቃድር አክለዉም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ የአከፋፈል መመሪያው ተግባራዊ እንዲደረግ ደብዳቤ መላኩን ተናገረዉ የመስከረም ወር ክፍያ እንደሚፈፀም እና የደሞዝ ጭማሪዉን ማዕከል በማድረግ ልዩነት እጅግ ቢዘገይ እስከ ጥቅምት 15 ድረስ ክፍያ እንደሚፈፀም ገልፀዋል፡፡
የመስከረም ወር ደሞዝ በአብዛኛው ክፍያ የተፈፀመ በመሆኑ በዚህ ወር የሚከፈለው ልዩነት መሆኑን እና ከጥቅምት ወር ጀምሮ ጭማሪን አማክሎ አንድላይ እንደሚከፈል ተቋማት ልዩነቱን አምጥተው ክፍያውን መፈፀም እንደሚችሉ ገለፃ መሰጠቱን ቢሮዉ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታቋል፡፡
መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከመስከረም ወር ጀምሮ በወሰነዉ የደመወዝ ማሻሻያ መሰረት ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ከብር 4ሺህ760 ወደ ብር 6ሺህ ሲያድግ ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21ሺህ492 ወደ ብር 39ሺህ ብር አግጓል፡፡
ለዚህም ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት እንደሚስፈልግ እና ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር እንደሚያደርሰው የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ነሀሴ 12 ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል ፡፡