የሳይበር ደህንነት ከሀገር ሉዓላዊነት ተለይቶ አይታይም ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሀይ ጳውሎስ ገለፁ

You are currently viewing የሳይበር ደህንነት ከሀገር ሉዓላዊነት ተለይቶ አይታይም ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሀይ ጳውሎስ ገለፁ

AMN- ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም

የሳይበር ደህንነት ከሀገር ሉዓላዊነት ተለይቶ አይታይም ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሀይ ጳውሎስ ገለፁ።

6ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንንት ወር የሳይበር ደህንነት ለኢትዮጵያ መሰረት በሚል መሪ ሀሳብ በይፋ ተጀምሯል።

ባለፉት 5 ዓመታት ወርሃ ጥቅምት ሲገባ ወሩን በሙሉ የሳይበር ደህንነትን በተመልከተ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ሲሰራ እንደነበር ይታወቃል ። ዘንድሮም በተመሳሳይ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ግንዛቤ የሚፈጠርበት የሳይበር ደህንነት ወር በይፋ ተጀምራል።

በማስጀመሪያ መርሃግብሩ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሀይ ጳውሎስ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬከተር ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የሳይበር ደህንነት ከሀገር ሉዓላዊነት ተለይቶ አይታይም ያሉት የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሀይ ጳውሎስ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠናቀቁም ይሁን የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለመጠበቅ የሳይበር ደህንነት ቁልፍ በመሆኑ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ሀሰተኛ መረጃ ከ5ቱ ዋነኛ የዓለም የሳይበር ደህንነት ስጋቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን ያነሱት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬከተር ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ፣ ሀሰተኛ መረጃን መከላከል የሁሉም ዜጎች ኃላፊነት ስለመሆኑ አስገንዝበዋል።

አስተዳደሩ የሀገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ከፍ የሚያደርጉ እና የዲጀታል ሉዓላዊነትን ለማርጋገጥ የሚስችሉ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝም ዋና ዳይሬክተሯ ገልፀዋል።

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በስኬት ተጠናቆ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትግበራ መጀመሩም በመድረኩ ተነስቷል።

በአሰግድ ኪ/ማርያም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review