የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 አስፈፃሚ ቦርድ ምርጫ መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ የዕውቅናና ምሥጋና መርሐ ግብር እያካሄደ ነው

You are currently viewing የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 አስፈፃሚ ቦርድ ምርጫ መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ የዕውቅናና ምሥጋና መርሐ ግብር እያካሄደ ነው

AMN – ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ምርጫ መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ በአድዋ መታሠቢያ አዳራሽ የዕውቅናና የምሥጋና መርሐ ግብር እያካሔደ ይገኛል፡፡

መርሀ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ እጅግ ታሪካዊ የሆነው የመጀመሪያው ምርጫ በመደረጉ ሁሉም ህዝበ ሙስሊም አላህን ሊያመሠግን ይገባል ብለዋል።

ምርጫው ሰላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ትልቅ ድርሻ ለነበረው መንግስት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ ህብረተሰቡ በነቂስ በመውጣት ላደረገው አስተዋፆም ምስጋና አቅርበዋል።

የዘንድሮ ምርጫ ፍትሃዊና ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላችውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ ምስጋና ይገባል ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ አመራሮች፣ ዑለማ፣ የመገናኛ ብዙኃን ኀላፊዎችና ሌሎችም ተገኝተዋል።

በ- መሐመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review