የሲቪል ምዝገባ ዘመናዊ ማህበረሰብን ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የኢሚግሽንና የዜግነት አገልግሎት ገለፀ

You are currently viewing የሲቪል ምዝገባ ዘመናዊ ማህበረሰብን ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የኢሚግሽንና የዜግነት አገልግሎት ገለፀ

AMN- ጥቅምት 01/2018 ዓ.ም

የሲቪል ምዝገባ ዘመናዊ ማህበረሰብን ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ገልፀዋል፡፡

የሲቪል ምዝገባና ቫይታል ስታቲስቲክስ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ ለ8ኛ ጊዜ በጅማ ከተማ “የሲቪል ምዝገባ ለህብረተሰቡ የዲጂታል መሰረተ ልማትና ሕጋዊ ማንነት ሥርዓት መሰረት ነው” በሚል መሪ ሀሳብ በመከበር ላይ ነው።

ከዜጎች ምዝገባ የሚገኙ መረጃዎች ወንጀልን ለመከላከል፣ መልካም አስተዳደር ለማስፈን፣ ለሀገር ደህንነትና ለፍትሀዊ ተጠቃሚነት ጉልህ ሚና እንዳላቸው የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ገልፀዋል።

የዜጎችን የልማት የተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ሌሎችንም ጥያቄዎች በተገቢ ሁኔታ ለመመለስ የዜጎች ምዝገባ ጉልህ ሚና እንዳለው የተናገሩት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ፤ የሲቪል ምዝገባና ቫይታል ስታትስቲክስ የኢትዮጵያን የ10 አመት የልማት እቅድ እና የአጀንዳ 2030 እቅድን ለማሳካት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ በበኩላቸው የሲቪል ምዝገባና ቫይታል ስታትስቲክስ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የድርሻው ሊወጣ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በ- አሸናፊ በላይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review