ወደ ዪናይት ኪንግደም ያቀናው የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ልዑክ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአየር ላንድ ሪፓቢሊክ እና በሌሎች አውሮፓ ሀገራት ከሚኖሩ የኢትዮጵያዊያን ዳያሰፖራ አባላት አጀንዳዎችን ተቀብሏል።
ኮሚሽኑ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአየር ላንድ ሪፓቢሊክ እና በሌሎች አውሮፓ ሀገራት ከሚኖሩ የኢትዮጵያዊያን ዳያሰፖራ አባላት ዛሬ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 11/2025 ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም አጀንዳ ያሰባሰበበትና የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተወካዮችን ያስመረጠበት መድረክ በለንደን ከተማ ሲያካሂድ ውሏሎ።
የምክክር መድረኩ በስኬት ተጠናቆ ተሳታፊዎች በቡድን ውይይት ያደራጇቸውንና ያጠናቀሯቸውን አጀንዳዎች ቦታው ለተገኙ ኮሚሽነሮች አስረክበዋል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ በቅርቡ በሚካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ወኪሎችንም መርጠዋል::
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገ/ስላሴ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር የዳያስፖራ አባላቱ በምክክሩ ላደረጉት ንቁ ተሳትፎ በኮሚሽኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በኮሚሽኑ የአሠራር ሥርዓት መሠረት በዚህ መድረክ የተሰበሰቡ አጀንዳዎችም ከሌሎች አጀንዳዎች ጋር በኮሚሽኑ ምክር ቤት ተቀርፀው ለሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ግብዓት እንዲሆኑ የሚደረግ መሆኑን ኮሚሽኑ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።