ባለስልጣኑ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ 2 ድርጅቶችን 600 ሺህ ብር መቅጣቱን አስታወቀ

You are currently viewing ባለስልጣኑ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ 2 ድርጅቶችን 600 ሺህ ብር መቅጣቱን አስታወቀ

AMN ጥቅምት 01/2018 ዓ/ም

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ 2 ድርጅቶችን እያንዳንዳቸውን 300 ሺህ ብር በድምሩ 600 ሺህ ብር መቅጣቱን አስታወቀ ።

ድርጅቶቹ ሮያል ከረሚላ ፋብሪካ እና ዲኤም ሲ ሪል እስቴት ሲሆኑ ባልተገባ መንገድ ከፋብሪካ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ሲለቁ በመገኘታቸው ቅጣቱ ተላልፎባቸዋል ።

በክፍለ ከተማው የኮሪደር ልማት እየለማ በሚገኝበት ጀሞ ወረዳ ፣ለቡ ወረዳ እንዲሁም ወረዳ 12 መዳረሻውን ያደረገው በተለምዶ አርሴማ ወንዝ አካባቢ የተለቀቀ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ፈሳሽ መሆኑ ተመላክቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለትን ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት ተቀጥተዋል ።

ባለስልጣኑ አሁን ላይ በወንዞች ዳርቻ ልማት መርሃ ግብር መሰረት የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማት ለከተማዎ ነዋሪዎች ምቹና ሳቢ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሆነ ማስታወቁን

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review