በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የክልባቲ ራሱ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ከትናንት ጀምሮ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ አጋጥሞታል።
በክልባቲ ራሱ ዞን የበራህሌ ወራዳ አስተዳዳሪ አቶ አሊ ሁሴን ለኤኤምኤን እንዳሉት በመሬት መንቀጥቀጡ አንድ የ12 አመት ህጻን ሲሞት ሌሎች 6 ሰዎች ቆስለዋል ብለዋል።
በአደጋዉ በተለይ በቡሬ እና አስ ጉቢ አላ ቀበሌዎች በንብረትና በሰው ላይ ጉዳት ማድረሱንም ተናግረዋል።
ተጎጂዎቹ ወደ ጤና ተቋማት እየተወሰዱ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።
በመሀመድ ማአር