የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ሥራ አስጀምረዋል።
ኢንስቲትዩቱ በትምህርት ዘርፉ የሚስተዋሉ የተደራሽነት ውስንነቶችን ከመፍታት ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለዉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገልጸዋል።
በሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይም ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰዓዳ አብዱረህማን፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)፣ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች: አባ ገዳዎች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡