አዲሱ ዓመት ኢትዮጵያ በምሽት ፀሀይ ያወጣችበት ከማይጨበጥ ወደ ሚጨበጥ ተስፋ የተሸጋገረችበት አመት መሆኑን የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት ገለጹ፡፡
3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ በአድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል ፡፡
የምክር ቤቱ አባላት ኢትዮጵያ ከማይጨበጥ ወደ ሚጨበጥ ተስፋ እየተሸጋገረች መሆኗን በመግለጽ አዲሱ አመት ትልልቅ ብስራቶች የተበሰሩበት እና ይፋ የተደረጉበት መሆኑንም አንስተዋል ።
በአድዋ ድል መታሰቢያ ሆነን ስለሁለተኛው አድዋ ድል አለማውራት ከባድ ነው ያሉት የምክር ቤቱ አባላት ፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የዘመኑ ዳግማዊ አድዋ ነዉ ሲሉ ገልፀውታል።
የመቻል፣የመፈፀም የትውልድ ቅብብሎሽ የታየበት መሆኑን አስረድተው፣ሰፊ ፕሮጀክቶች በሀገር እና በከተማ ደረጃ መጀመሩ ትልቅ ተስፋ መሆኑን አመላክተዋል።
አዲስ አበባ የታላላቅ አህጉርና አለም አቀፍ ስብሰባዎች መዳረሻና የቱሪዝም ማዕከል መሆኗን ጠቅሰው፣ ይህ የሆነው የከተማዋ አመራሮች 24/7 በመስራታቸው መሆኑን ተናግረዋል ።
ከተማዋ ለዚህ ስኬት በመድረሷ አመራር እና ነዋሪዎች ልማቱ እንዲሳለጥ ላደረጉት አስተዋፅኦ የምክር ቤቱ አባላት ምስጋና አቅርበዋል።
በ-ሔለን ተስፋዬ