በአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ስራ የመዲናዋን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ገጽታ የቀየሩ ስራዎች የተሰሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት ገለጹ፡፡
3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ በአድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት ከጥቂት አመታት በፊት አዲስ አበባ ምንም አይነት ከተሜነት የማይስተዋልባት የሰፋፊ ከተሞች ስብስብ ትመስል እንደነበር ገልፀው፤ ዛሬ ላይ እጅግ መለወጧን ጠቅሰዋል።
ከቅርብ አመታት ወዲህ በመዲናዋ የተሰሩ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች የመዲናዋን ገጽታ ሙሉ በሙሉ መቀየራቸዉን ተናግረዋል፡፡

አዲስ አባባ ሌሎች ከተሞች አንብበው የሚረዷትና የሚማሩባት ከተማ ነች ያሉት የምክር ቤቱ አባላት የአፍሪካዊያን ተስፋ እንደሆነችም መረጃዎችን ጠቅሰዉ ተናግረዋል፡፡
ከተማዋ ለዚህ ስኬት መድረሷ እና ሌሎች የሀገሪቱ ከተሞችም የሷን ፈለግ ተከትለው እያደጉ ስለመሆናቸው ያነሱት የምክር ቤቱ አባላት ይህም የመዲናዋ ብቻ ሳይሆን የሀገር ገጽታ የቀየረ ተግባር መሆኑን አመላክተዋል።
በ- ፍሬህይወት ብርሃኑ