የከተማዋን የትራንስፖርት አገልገሎት ለማዘመን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

You are currently viewing የከተማዋን የትራንስፖርት አገልገሎት ለማዘመን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

AMN – ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም

‎የከተማዋን የትራንስፖርት አገልገሎት ለማዘመን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል፡፡

ትራንስፖርት አገልግሎት ለከተማዋ ለነዋሪዎች በአግባቡ ለመስጠት ከፍተኛ የሆነ የከተሜነት ፍልሰት ተፅዕኖ መፍጠሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

ይህንን የገለፁት 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን በአድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አደራሽ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ነው፡፡

‎በዚህ ጉባዔ ላይ ከነዋሪዎች የተሰበሰቡ ጥያቄዎች መካከል ስለትራንስፖርት አገልግሎት ጥያቄ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት፤ የበዓል ሰሞን እና ምሽትን ተገን በማድረግ በሚስተዋሉ የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪዎች ነዋሪዎች መማረራቸውን አንስተዋል። ከተማ አስተዳደሩ ይህንን እና መሰል ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ምን አስቧል ሲሉ የነዋሪዎችን ጥያቄ አቅርበዋል።

‎ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሰጡት ምላሽ፣ ትራንስፖርት በማዘመን በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው፤ይሁን እንጂ የትራንስፖርት አገልግሎት ለነዋሪዎች ለመስጠት ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ፍልሰት መኖሩን አመላክተዋል።

‎ይህ ተፅዕኖ ከትራንስፖርት በተጨማሪ የውሀ፣ መብራት፣ ትምህርት ላይ ከፍተኛ የሆነ የአገልግሎት ፍላጎቶች መኖሩን ገልፀዋል። የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሳለጥ የአንድ ማዕከል የትራፊክ ስምሪት ስርዓት ለማስጀመር በሂደት ላይ እንደሚገኝም ከንቲባዋ አስረድተዋል።

‎በ- ሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review