የኢትዮጰያ ብስራቶች በወርሃ መስከረም 

You are currently viewing የኢትዮጰያ ብስራቶች በወርሃ መስከረም 

AMN – መስከረም 3ዐ/2018 ዓ.ም

‎በኢትዮጰያውያን ዘንድ መስከረም ብስራት ናት ። የስኬት ማረጋገጫ የዕቅች ሚዛን መድፊያ  ጭምር ናት ወርሃ መስከረም ። ወርሃ መስከረም በግለሰብም በአገርም ትልቅ ቦታ ይሰጣታል ምክኒያቱም  ብዙሀኑ ውጥናቸውን  የሚጀመሩበት ወቅት መሆኑ እሙን ነው ።

‎በ2018 ዓ.ም መግቢያ ብቻ ኢትዮጵያ ለሀገሬው ፣ለጎረቤትም፣ ለዓለምም ብዙ ብስራቶችን ይዛ ብቅ ብላለች ። በኢትዮጵያው  በመስከረም ወር  ብቻ  የተከናዋኑ  ዋና ዋና አገራዊ  ክዋኔዎች   የኤ ኤም ኤን ዲጅታል በወፍ በረር እንዲህ ቃኝተናል ።

ልማትን በተመለክተ

በሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር  መመረቁ የወርሃ መስከረም ትሩፋቶች ውስጥ አንዱ ነው ።

‎በአመት 1.33 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን ዙር  በዕለቱ የተጀመረ ሲሆን ፣ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1‚000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል ።

‎ከሁሉም በላይ ፕሮጀክቱ የጋዝ ማምረቻ ብቻ ሳይሆን  ለማዳበሪያ ማምረቻ ወሳኝ የሆነውን ግብዓት በማቅረብ ለምግብ ሉዓላዊነት ጥረት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ  እንደሚያገለግል ታውቋል። በማህበራዊ ጉዳይ  አነጋጋሪ ከሆኑ ጉዳዮች ውስጥ  የመንግስት ሰራተኞች  የደመወዝ  ጭማሪ  ይገኝበታል ።

በወርሀ መስከረም ሌላኛው አበይት አገራዊ ተግባራት በሀላባ እና ከምባታ እንዲሁም በሀዲያ እና ስልጤ ዞኖች የተገነቡትን  የሞዴል የገጠር መንደሮችን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስረከባቸው  ነው  ።

‎በእነዚህ መንደሮች   ባለሶስት መኝታ ቤት መኖሪያዎች ለማብሰል የሚያገለግል የባዮጋዝ መሣሪያ፣ የፀኃይ ኃይል ማመንጫ፣ የዶሮ ማርቢያ፣ የተለየ የእንስሳት በረት የተሟላላቸው መሆናቸው ተገልፃል ። በገጠር ቀበሌዎች ተግባራዊ  አነስተኛ ወጪ ከአካባቢ በሚገኙ ግብዓቶች የተሻለ መኖሪያ ከማስገኘት አንፃር ለገጠሩ ማኅበረሰብ ብልጽግና ያለውን አስተዋፅኦ  የሚያሳይ ነው ተብሏል ።

ኢኮኖሚ

የአዲሱ የመንግስት ሰራተኞች  የደመወዝ ስኬል  ይፋ መሆኑ  መንግስት የኑሮ ውድነቱን  ተፅዕኖ ለማቃለል እንደሚያደርግ እና በመስከረም ወር ወደ ተግባር ከተገቡ አሰራሮች ግንባር ቀደሙ ነው። የወርሃ መስከረም ሌላኛው ብስራት የመደመር መንግሥት መፅሀፍ ለአንባቢያን መቅረቡ ሲሆን በመደመር ስያሜ ከወጡ መፅሕፍት መካከል 4ኛው ነው

ሌላኛው የመስከረም ወር መገለጫ የሆኑና በጉጉት የሚጠበቁ የአደባባይ በዓላት ግንባር የሁኑት  የመስቀል እና ኢሬቻ በዓል ተጠቃሽ ናቸው  ።  በእነዚህ በዓላት  የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ቱሪስቶች በበዓሉ ታድመዋል በዓላቱም በአንድነትና በድምቀት ተከብረው ተጠናቀዋል ።

ሌላኛው በወሩ ከተከናወኑ ሁነቶች አንዱ የ7ኛው የታማኝ ግብር ከፋይ እውቅና ሥነ-ሥርዓት ተሸላሚዎች  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተከናውኗል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣የምታዋጡት ግብር ለጋራ እድገት እና ለሕዝባዊ ጠቀሜታ በሚውሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚውል ቃል ገብተን ነበር ብለዋል።

‎”ዛሬ በከተማች ኮሪደሮች የሚታየው ለውጥ ለዚያ ቃላችን ሕያው ምስክር መሆኑን  አስታውሰው፣የዛሬ ጥረታችሁ የነገን ትውልድ የተሻለ መፃኢ እድል እየቀረፀ ነው ሲሉ    አመላክተዋል።

‎ይህ ፕሮጀክት እውን መሆኑ እንደ ማኅበረሰብ አዲስ ሀሳቦች ሲፈልቁ “አይቻልም” በሚለው የቆየ አስተሳሰብ የመፈተን ተግዳሮት ቢኖሩም ዜጎችን  መለውጥ እንደሚቻል ሀብቶችን ወደ ትክክለኛ ትኩረቶቻችን ካዋልንም ማኅበረሰብን በርግጥም ማሻገር እንደሚቻል በአራቱ ዞኖች የተሠራው ሥራ በመላው ክልሉ መደገም እንደሚኖርበት ጠቅላይ ሚንስትሩ በምረቃ ስነ-ስርአቱ ያሳሰቡበት ሳምንት ነበር ።

ዲጂታላይዝሽንና ሚዲያ

የPulse of Africa ሚዲያ ሥራ መጀመር አፍሪካን በአሉታዊ ገጽታ የማቅረብ ሥራን ለመመከት እና  አገራዊ  ትርክት በራስ አቅም የመቅረጽ ተግባር የሚያፀናበት ጠቃሚ እርምጃ መባሉ ተገልጿል ።

‎አፍሪካ ሰፊ እና እምቅ ሀብት ያላት አኅጉር ብትሆንም አብዛኛውን ጊዜ እንደ አነስተኛ እና አቅመቢስ ተደርጋ እንደምትሳል ፣ በዚህ የተነሳ  አነስተኛ ግን እጅግ ትርጉም ያለው የPulse of Africa ጅማሮ በመጪዎቹ ጊዜያት ከፍ ወዳለ መሪ አኅጉራዊ ሚዲያ የማደግ መንገድ እጅግ ጠቃሚ ጠቅላይ ሚንስትሩ በትስስር ገፃቸው መግለፃቸው ይታወሳል ።

በዲፕሎማሲ ረገድ በወርሃ መስከረም ከተሰሩ ሰራዎች መካከል ፡-

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በተለያዩ ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት  አጠቃላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆኑ እነዚህም የኃይል ማመንጫ፣ ግብርና፣ የጤና ጥበቃ ልማት እና የመከላከያ ትብብርን ያካትታሉ። 

ለማኅበረሰብ አገልግሎት የሚውል ንፁህ ኃይል ለማቅረብ የጋራ የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ ለማልማት ስምምነቶችን በመፈራረም የጋራ ፍላጎቶቻችንን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች  ከስምምነት መድረሱ ይታወቃል።

ሌላኛው አህጉራዊ ሁነት በኬንያ ናይሮቢ   በተካሄደው 24ኛው የCOMESA መሪዎች ጉባኤ ላይ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የአፍሪካን የኢኮኖሚ ታሪክ የመቀየር ልዩ እድል  መፍጠሩን ጠቅላይ ሚንስትሩ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ተገኝተው  መልእክት  ማስተላለፋቸው  ይታወሳል ።

‎እንደ አኅጉር ጥረቶች ለማጣመር እና ቀጣናዊ ትስስሮችን ለማፋጠን ክህሎቱ እና መሠረት መጣሉን አመላክተዋል።

‎በኢትዮጵያ ዲጂታል ክህሎትን ለማበልጸግ እና አስፈላጊ መሠረተ ልማት ለመገንባት ጥሩ እርምጃዎች መራማዷን ፣የጋራ ዲጂታል ነገን ለማሳደግ በትብብር ለመሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

‎በCOMESA   ትግበራዎች መካከል ኢትዮጵያ በአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና መገበያየት መስከረም በይፋ  ጀምራለች ።

‎በነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነቱ መሰረት የኢትዮጵያ ምርቶች የመጀመሪያው ግብይት ኤክስፖርት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ካርጎ ተርሚናል  በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል፡፡

‎የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር  ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)፣ ይህ ንግድ መጀመሩ የሀገራችን ወጪ ንግድ መስፈንጠር የጀመረበትን ሂደት ይበልጥ ሊያሳልጥ ይችላል መባሉን፣ በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ተናግረዋል ፡፡

በመርሃ ገብሩ ስጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና ጫት ወደ ሶማሊያ፣ ነጭና ቀይ ቦሎቄ እንዲሁም ቡና ወደ ደቡብ አፍሪካ፣ የበቆሎና የቦሎቄ ምርቶች ወደ ኬንያ የመላክ ሰራ ተከናውኗል።

‎ይህም ኢትዮጰያ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ በጋራ የማደግ እና የመበልጸግ ውጥኗ የመተግበር ጅማሮ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review