የተጠናቀቁና የተጀመሩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የኢኮኖሚ ስብራቶቻችንን የሚጠግኑና የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታን የሚጨምሩ መሆናቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ፡፡
18ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተቋም ውስጥ በድምቀት ተከበሯል።
የጥቁር ሕዝቦች ድልና ኩራት ከሆነው ዓድዋ ድል ቀጥሎ ዳግማዊ ዓድዋ የሆነው የሕዳሴ ግድባችን በማጠናቅቅና የዘመናት የኢኮኖሚ ስብራቶቻችን ሊጠግኑ የሚችሉ የጋዝ ማውጣት፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ሥራ መጀመራቸው፣ የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታን የሚጨሚሩ መሆናቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ተናግረዋል፡፡
የተጀመሩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶቻችንና የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች የሰንደቅ ዓላማችንን ክብር ከፍ የሚያደርጉ ናቸው ያሉት ሚኒስትሯ፤ የመንግሥት ኮሙኒኬሽ አገልግሎት አመራሮችና ባለሙያዎች ከሁሉም በላይ ከፊት በመሰለፍ ሀገራዊ የብልጽግና ጉዞያችንን በማሳካት ረገድ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡
በዕለቱም 18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አስመልክቶ የተዘጋጀው ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓጎታል፡፡
በሰነዱም የሀገረ መንግሥት ግንባታ፣ የኢፌዴሪ የሰንደቅ ዓላማ ምንነት፣ በሰንደቅ ዓላማ የተቀመጡ ሕጋዊ ማዕቀፎች፣ በሰንደቅ ዓላማ አጠቃቀም ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ “ሰንደቅ ዓላማችን የሉዓላዊነታችን መገለጫ፣ የአንድነታችንና መሰባሰቢያችን ጥላ መሆኑን በመረዳት ለሰንደቅ ዓላማው ክብር መስጠት አለብን” ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ተናግረዋል፡፡
ሰንደቅ ዓላማው የሀገርና የሕዝብ የክብር ምልክት መሆኑን ተረድተን ስኬቶቻችንን በማጉላት የሰንደቃችን ክብር ከፍ በሚያደርጉ ሀገራዊ ውጥኖች ላይ ዓቅማችንን ማዋል ይጠበቅብናል ሲሉ አክለው ገልፀዋል፡፡
በሥነ-ሥርዓቱም ላይ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች መገኘታቸውን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።