ዌልስና ቤልጂየም ባደረጉት ጨዋታ ወደ ሜዳ የዘለቀችዉ አይጥ

You are currently viewing ዌልስና ቤልጂየም ባደረጉት ጨዋታ ወደ ሜዳ የዘለቀችዉ አይጥ

AMN ጥቅምት 4/2018

ዌልስና ቤልጂየም ባደረጉት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ አንዲት አይጥ ወደ ሜዳዉ ዘልቃ መግባቷ ብዙዎችን አስደምሟል፡፡

ቤልጂየም ዌልስን 4 ለ 2 በሆነ ዉጤት ባሸነፈችበት በዚህ ጨዋታ አይጧ በ65ኛ ደቂቃ ወደ ሜዳ በመግባቷ ጨዋታዉ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ተቋርጧል፡፡ የጀርመን ዜግነት ያላቸዉ የእለቱ ዳኛ ዳንኤል ሳይበርት አይጧ ወደ ሜዳዉ ዘልቃ መግባቷን ካረጋገጡ በኋላ ተመልሳ እስከምትወጣ ጨዋታዉን አስቁመዋል፡፡

የዌልስ እና የቶተንሃሙ ተጫዋች ብሬናን ጆንሰን አይጧን ከሜዳ ዉስጥ ለማዉጣት ሲያደርግ የነበረዉ ጥረት በእግር ኳስ ታዳሚዎች ዘንድ ተዝናኖትን ፈጥሯል፡፡ የቤልጂየሙና የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂዉ ቲቦ ኮተርቶዋንስ በበኩሉ አይጧን በእጅ ይዞ ከሜዳዉ ዉስጥ ለማዉጣት ሲሞክር ከእጁ በማምለጥ አስቸግራዉ እንደነበር ዘ ሰን አስነብቧል፡፡

ለተወሰኑ ደቂቃዎች ያህል የታዳሚዎችም ሆነ የካሜራ አይኖች በአይጧ ላይ ያተኮረ ቢሆንም ከቆይታዎች በኋላ አይጧ በገዛ ፈቃዷ ሜዳዉን ለቃ ወጥታለች፡፡ በእለቱ የተፈጠረዉን ክስተት ተከትሎ አንዳንድ ደጋፊዎች ፈገግ የሚያሰኙ አስተያየቶችን ሰንዝረዋል፡፡

በኮርቶዋ ላይ የተቆጠረችዉ ግብ የአይጧ ጎል ነዉ ሲሉ ሌሎች ደግሞ አይጥ የእለቱ ድንቅ ተጫዋች (Man of the Match) ብለዋል፡፡ ከአሁን በፊት በኦልድትራፎርድ ሜዳ አይጥ በመታየቷ በርካቶችን ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡

አይጥን ጨምሮ ድመትና ዉሻ ከአሳዳጊዎቻቸዉ እጅ በማምለጥ ወደ ሜዳ ሲገቡ መመልከት የተለመደ ክስተት ነዉ፡፡ ይህም በዉጥረት ዉስጥ ላሉ ደጋፊዎች ተጨማሪ ተዝናኖትን የሚፈጥር ነዉ፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review