የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 49ኛ መደበኛ ስብሰባ የኒውክለር ኮሚሽን እንዲቋቋም ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ምክር ቤቱ በስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተወያየ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኒውክለር ኃይል ኮሚሽን ማቋቋሚያ ደንብ አንዱ ጉዳይ ነበር፡፡
ኮሚሽኑ ሀገራችን የኒውክለር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ መንገድ ከዓለም አቀፍ ማዕቀፎች ጋር በተጣጣመ መልኩ በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በምግብ ዋስትና፣ በጤና አገልግሎት፣ በሳይንስ እና ምርምር ዘርፎች ላይ ለመጠቀም የምታደርገውን ጥረት የመምራትና የማስተባበር ሃላፊነት እንዲኖረው ተደርጎ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱም በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡