ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

You are currently viewing ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

AMN ጥቅምት 4/2018

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ዛሬ ተቀበሉ።

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ በብሔራዊ ቤተ መንግስት በተካሄደው ሥነ ስርዓት ላይ የተለያዩ አገራትን አዳዲስ አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል።

ለፕሬዚዳንት ታዬ የሹመት ደብዳቤያቸወን ካቀረቡት መካከል የሞሪታኒያ አምባሳደር ኢል ሀውሴን ኦልድ ናጊ፣የካዛኪስታን አምባሳደር ዣልጋስ አዲልባየቭ ፣ የቫቲካን አምባሳደር ብሬን ኦዲጊግዊ፣የባንግላዲሽ አምባሳደር ኤር ቫይስ ማርሻል ሲትዋት ናዬም እና የዐረብ ሊግ አምባሳደር መሐመድ ኦማር አል ማርሆን ይጠቀሳሉ።

በተመሳሳይ የኢንዶኔዥያው አምባሳደር ፋይዝል ቸሪይ ሲዳርት፣ የሰርቢያ አምባሳደር ዳቮር ትርኩልጃ እና የስዊድኑ አምባሳደር ማኙስ ሌናርትሶን የሹመት ደብዳቤያቻውን አቅርበዋል።

በተጨማሪም የካናዳው አምባሳደር ኒኮላስ ሲማርድ፣ ሲውዘርላንድ አምባሳድር ሪካረድ ቻንዳ፣ የግብጹ አምባሳደር ኦባይዳ ኢል ዳንዳራውይ፣ የሀንጋሪው አምባሳደር አቲላ ቶዝ፣ ሳን ማሪያኖ አምባሳደር ፔሮ ስካርፔሊኒ እና የቱሪክሜንስታን አምባሳደር መካን ኢሻነጉሊየብ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review