ሴኔጋል እና ኮትዲቯር ለዓለም ዋንጫ ማለፍ ቻሉ

You are currently viewing ሴኔጋል እና ኮትዲቯር ለዓለም ዋንጫ ማለፍ ቻሉ

AMN-ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም

በአፍሪካ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሴኔጋል እና ኮትዲቯር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

ምድብ ሁለትን በበላይነት ያጠናቀቀችው ሴኔጋል ሞሪታኒያን 4ለ0 አሸንፋለች።

ሳዲዮ ማኔ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ፣ ኢሊማን እንዳዬ እና ሀቢብ ዲያሎ ሌሎቹን ግቦች አስገኝተዋል።

ሴኔጋል ከ10 ጨዋታ 24 ነጥብ በማግኘት በበላይነት ማጠናቀቅ ችላለች።

ምድብ ስድስት ላይ የነበረችው ኮትዲቯር ኬንያን 3ለ0 በማሸነፍ በዓለም ዋንጫው ሌላኛዋ የአፍሪካ ተወካይ ሆናለች።

ለኮትዲቯር ፍራንክ ኬሲ ፣ ያን ዲዮማንዴ እና አማድ ዲያሎ ሦስቱን ግቦች አስቆጥረዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review