ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ያስመረቅነው ባለ 15 ወለል ዘመናዊ የሲኒማ ማዕከል በአይነቱ ልዩና ለኪነጥበብ እድገት አዲስ ምዕራፍ ከፋች መሆኑን ሳበስር በደስታ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
መንግስት የኪነጥበብን ወሳኝ ሚና በመረዳትና ልዩ ትኩረት በመስጠት በቢሊዮኖች በጀት መድቦ በአይነታቸው ልዩና ዘመናዊ ለሲኒማ ፣ለቲያትር ራሳቸውን የቻሉ ትልልቅ ማዕከላት ሲገነባ ፤ በኪነጥበብ ዘርፈ የተሰማራችሁ ከያኒያንና የጥበብ ቤተሰቦች ሁሉ፣ ለአገራችን ሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ መሰረት የሚሆኑ የጥበብ ስራዎችን በማበርከት፣ ታሪክ የማይዘነጋው ዘመን ተሻጋሪ አስተዋጽኦ እንደምታበረክቱ በማመን ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።