በአዲስ አበባ የተገነቡ የጥበብ ማዕከለት፣ ዓለም አቀፍ ደረጃን ያሟሉና የሀገራችንን የጥበብ ሥራዎች ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ መሆናቸውን የባህልና ስፓርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ገልፃዋል፡፡
የጥበባት ዘርፍ የሀገር ገጽታን የሚገነቡ፤ የማህበረሰብ ብያኔን የሚሰጡ፣ ለባህል ልውውጥና ዲፕሎማሲ ዕድገት ቁልፍ ሚና የሚጫወት ዘርፍ ነው።
በአዕምሯዊ ልማትና ብልጽግና ላይ ጥበባት ያላቸውን ፋይዳ በመረዳት መንግስት ለዘርፉ ዕድገት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ሚኒስትር ሽዊት ተናግረዋል።
በመላው ሀገሪቱ እየተሰራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራዎች፤ የገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ውስጥ የጥበባት ማቅረቢያ ስፍራዎች በዕቅድ ተይዞ እንዲሰራ ተደርጓል ብለዋል።

በተለይ ደግሞ በመዲናችን አዲስ አበባ የተገነቡ የጥበብ ማዕከለት፣ ዓለም አቀፍ ስታንዳርድን ያሟሉና የሀገራችንን የጥበብ ሠራዎች ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ መሆናቸውንም ገልፀዋል።
በልዩ ሁኔታ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ፣ ሁለት ትላልቅ የጥበብ ማዕከላትን በማስመረቅ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለሰጡት አመራርና ትኩረት ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
ከያኒያንም ይህንን ዕድል በመጠቀም ህዝብን የሚያቀራርብ፤ አብሮነትን የሚያጠናክር፤ለህብረብሄራዊ አንድነትና ለህዝቦች ትስስር አስተዋጾ የሚያበረክት፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን አጉልቶ የሚያሳይ፤ የጥበብ ሥራዎችን የማቅረብ ሀገራዊ ሀላፊነት ስላለብን፣ ይህንን የሚመጥን ሥራ መስራት እንደሚገባም የባህልና ስፓርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ መግለፃቸውን ከከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡