በከተማዋ መኪና በማቆም ሽንት የሚሸኑ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስጠነቀቀ፡፡
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ከዋናው አየር መንገድ ልዩ ስሙ ወሎ ሰፈር አካባቢ መኪና በማቆም በኮሪደር ልማት ላይ ሽንት በመሽናት ያመለጠ ግለሰብ ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል በፈፀመው የደንብ መተላለፍ መሰረት 2ሺህ ብር መቅጣቱን ባለስልጣኑ አስታዉቋል፡፡
አዲስ አበባን ውብና ፅዱ ለማድረግ የተያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ መሰል ደንብ መተላለፎች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡
ደንብ ተላላፊዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስቧል።