ከዚህ ቀደም የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሳይኖራችሁ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላችሁ ግብር ከፋዮች ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥራችሁን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር በአካል መሔድ ሳይጠበቅብዎ ይህን ሊንክ https://mor-migration.fayda.et በመጠቀም ማያያዝ ይችላሉ።
ይህን በማስተሳሰርዎ ፡
– ግብር በሚከፍሉበት ወቅት ጊዜዎን መቆጠብ ይችላሉ ፤
– በኦንላይን የሚሰጡ አገልግሎቶችን ቀላል እንዲሆን እና
እንዳይጭበረበር ይረዳል።
ያስተውሉ፦
የግል መረጃዎ ደህንነት በእርስዎ እጅ ስለሆነ ፤ ፋይዳ ልዩ ቁጥር (FIN) በገቢዎች ለሚሰጡ አገልግሎቶች ያለምንም ችግር ማጋራት ይችላሉ።