የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) አመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን ከዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ልዑክ በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF) አመታዊ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
ከስብሰባው ጎን ለጎንም የኢትዮጵያ ልዑክ ከዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በውይይቱ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ እድገት ላበረከተው የረጅም ጊዜ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞ እና በሂደት ላይ ያለውን ሃገራዊ ምክክር ሂደት አድንቀው፤ አሁንም ሃገሪቱ ለምታደርገው የለውጥ ጉዞ ባንኩ ድጋፉን እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
በሊያት ካሳሁን