ከአመጋገብ ስርዓት ጋር የሚገናኘው የጉበት ህመም ከፍተኛ መጠን ያለው የስብ ወይም ቅባት በጉበት ላይ ሲታይ የሚፈጠር ህመም መሆኑን የስነ-ምግብና የህክምና ባለሞያዎች ይገልጻሉ፡፡
የስነ-ምግብና የህክምና ባለሞያ ኬብሮን ሰናይ ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ በርካታ የጉበት ህመም ዓይነቶች መኖራቸዉን ይናገራሉ፡፡

ከአመጋገብ ስርዓት ጋር በተገናኘ የሚፈጠረው የጉበት ህመም በአብዛኛው በዘይት የተጠበሱ፣ ጣፋጭ የሆኑ እና የታሸጉ ምግቦችን በማዘውተር የሚከሰት መሆኑን ነው የገለጹት ።
ህመሙን ለመከላከል የአመጋገብ እና የህይወት ዘይቤአችንን ማስተካከል እንደሚያስፈልግ እና ጤናማ እና በአግባቡ የበሰሉ ምግቦችን መመገብ፣ ተፈጥሮአዊ ይዘታቸውን የጠበቁ ምግቦች አትክልት እና ፍራፍሬዎች፣ ጥራጥሬዎችን በምግባችን በማካተት ጤናችንን መጠበቅና ህመሙን መከላከል ይቻላል ብለዋል።
በፍሬህይወት ብርሃኑ