AMN መስከረም 6/2018 ዓ.ም
ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ376 ሺህ 600 በላይ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች መዲናዋን መጎብኘታቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ብሩክ ታደሰ ለኤ ኤም ኤን እንደገለጹት፤ ከ2 ሚሊዮን 275 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች እና ከ376 ሺህ 600 በላይ የውጭ ሀገራት እንግዶች ከተማዋን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።
የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ደግሞ ለጎብኚዎች ቁጥር መጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው አቶ ብሩክ አንስተዋል።
በቱሪዝም እሴት ሰንሰለት ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ከዘርፉ ተጠቃሚ ስለመሆናቸውም ጠቅሰዋል።
በላይሁን ፍስሃ