የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢ እድገት ከለዉጡ ወዲህ እመርታዊ ለዉጥ እያስመዘገበ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ “ግብር ለሃገር ክብር ” በሚል መሪ ቃል ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እና ግብር ከፋዮች በተገኙበት የሽልማት እና የእውቅና መርሃ ግብር በአዲስ አለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢ እድገት ከለዉጡ ወዲህ እመርታዊ ለዉጥ እያስመዘገበ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በ2010 በጀት አመት መጨረሻ 33 ቢሊዮን ብር የነበረዉ የገቢ አሰባሰብ በ2017 በጀት ዓመት ወደ 233 ቢሊዮን ብር ማደጉን ተናግረዋል፡፡
የ2017 በጀመት አመት አፈጻጸም ከ2016 በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር በ87 ቢሊዮን ብር እድገት ማሳየቱንም ሃላፊው ገልጸዋል፡፡
ይህንን እመርታዊ ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ የሪፎርም ስራዎች መሰራታቸውን የገለፁት ሃላፊው፤ የገቢ እድገቱ እንዲመዘገብ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉንም ጠቁመዋል፡፡
በሊያት ካሳሁን