በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በቂ የሀብት ተደራሽነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ፍትሃዊ የሆነ የፋይናንስ ስርዓት እንዲፈጠር የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ ጥሪ አቅርበዋል።
ሚኒስትሩ ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን እየተካሄደ በሚገኘው 114ኛው የቡድን 24 አባል ሃገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች እና የብሔራዊ ባንክ ገዢዎች ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ለታዳጊ ሀገራት የረጅም ጊዜ ልማት ላይ ውጤት የሚያስገኝ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ስርዓት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስትሊና ጆርጂየቫ እና የዓለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በጉባኤው ላይ ተሳትፈዋል።
የገንዘብ ተቋሙ አመራሮች በቡድን-24 አባላት እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ጥረት አድንቀው፣ የፋይናንስ እና የኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማስጠበቅ ብሎም ለዘላቂና ሁሉን አቀፍ ዕድገት መሠረት ለመጣል የሚደረገው እገዛ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በዳዊት በሪሁን