የኘላቲኒየም እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ታማኝ ግብር ከፋዮች የ2018 ዓ.ም የንግድ ዘርፍ አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ግብር ለሃገር ክብር” በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀዉ የሽልማት እና እውቅና መርሃ ግብር ለታማኝ ግብር ከፋዮች እዉቅና ሰጥቷል፡፡

በመርሃ ግብሩ በየደረጃዉ ለሚገኙ ግብር ከፋዮች እዉቅና የተሰጠ ሲሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የገቢዎች ሚኒስትሯ ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ለታማኝ ግብር ከፋዮቹ የኘላቲኒየም ፤ የወርቅ ሜዳሊያ እና የብር ሚዳሊያ ሰጥተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የኘላቲኒየም እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ታማኝ ግብር ከፋዮችን የንግዱ ዘርፍ የ2ዐ18 አምባሳደር ሆነዉ መሾማቸዉን ተናግረዋል፡፡

አምባሳደሮቹ ከተማዋ በምታከናውናቸው ማንኛውም ኩነቶች የቅድሚያ የልዩ ክብር አገልግሎት እንዲሰጣቸው ከንቲባ አዳነች አቤቤ አብስረዋል፡፡
የብር ሜዳሊያ ደረጃ ተሸላሚዎች ለሆኑት ደግሞ በሚቀጥለው አመት ይህንን አኩሪ ድል ለመጐናፀፍ በርትተው መስራት እንደሚገባቸውም ጠይቀዋል፡፡
በ-በረከት ጌታቸው