ለወርቅና የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚዎች “የቪአይፒ” ፕሮቶኮልና ቅድሚያ አገልግሎት የማግኘት መብት ተሰጠ

You are currently viewing ለወርቅና የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚዎች “የቪአይፒ” ፕሮቶኮልና ቅድሚያ አገልግሎት የማግኘት መብት ተሰጠ

AMN ጥቅምት 6/2018

ለወርቅና የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚዎች “የቪአይፒ” ፕሮቶኮልና ቅድሚያ አገልግሎት የማግኘት መብት ተሰጠ።

የአዲስ አበባ ከተማ ታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅናና ሽልማት መርሐግብር ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለወርቅና የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚዎች ከተማዋ በምትሰጠው አገልግሎትና በምታከናውናቸው በየትኛውም ኩነቶች ውስጥ “የቪአይፒ” ፕሮቶኮል እና ቅድሚያ አገልግሎት የማግኘት መብት እንዲሰጣችሁ ወስነናል ሲሉ አብስረዋል።

በተጨም የወርቅና የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚዎች በ2018 በጀት ዓመት የግብር አምባሳደሮች መሆናቸውን አሳዉቀዋል። የብር ደረጃ ተሸላሚዎች በሚቀጥለው ዓመት የወርቅና የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ እንደምትሆኑ ተስፋ አደርጋለሁም ብለዋል።

ግብር የፍትሐዊነት ማስፈኛ መሳሪያ መሆኑን ገልጸው፤ በከተማዋ የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚደረጉ ድጎማዎች ከታማኝ ግብር ከፋዮች የተገኘ መሆኑን አንስተዋል። እኛ እናንተን የበለጠ ሀብታም ለማድረግ የጀመርነውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለንም ሲሉ መናገራቸዉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review