ሰሜን አሜሪካ ፣ ካናዳ እና እንግሊዝን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት የተከናወነው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በስኬት መጠናቀቁ ተገለፀ

You are currently viewing ሰሜን አሜሪካ ፣ ካናዳ እና እንግሊዝን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት የተከናወነው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በስኬት መጠናቀቁ ተገለፀ
  • Post category:ፖለቲካ

‎AMN መስከረም 7/2018 ዓ.ም

‎ሰሜን አሜሪካ ፣ ካናዳ እና እንግሊዝን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት የተከናወነው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።

‎ኮሚሽኑ በደቡብ አፍሪካ ፣ በሰሜን አሜሪካ ፣ በካናዳ ፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፣ በስዊድን እና በእንግሊዝ ስኬታማ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ማከናወኑ ተገልጿል።

‎የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ በሰጡት መግለጫ በስድስቱ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ያለምንም ገደብ በነፃነት ሃሳባቸውን ስለመግለፃቸው ተናግረዋል።

‎ከዲያስፖራው የማህበረሰብ ክፍል በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል ያሉት ቃል አቀባዩ፤ የተለየ አቋም ያላቸው ዜጎችም የተሳተፉበት ሂደት እንደነበር ገልፀዋል።

‎ተሳታፊዎች ሀገራዊ መግባባት ሊደረሰባቸው ይገባል ያሏቸውን አጀንዳዎች ለኮሚሽኑ ማቅረባቸውንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

‎አሁንም በምክክር ሂደቱ ያልተሳተፉ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በበይነ መረብ የመሳተፍ አማራጭ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

‎በትግራይ ክልል አሁንም ምክክር ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታዎች ለመፍጠር ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ በመግለጫው ተነስቷል።

‎በወንድምአገኝ አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review