‎መንግስት የህብረተሰቡን ችግር በቴክኖሎጂ በመታገዝ የሚፈታ ትውልድ ለመፍጠር የተለያዩ ተግባራትን ሲሰራ መቆየቱን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ

You are currently viewing ‎መንግስት የህብረተሰቡን ችግር በቴክኖሎጂ በመታገዝ የሚፈታ ትውልድ ለመፍጠር የተለያዩ ተግባራትን ሲሰራ መቆየቱን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ

AMN – ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም

መንግስት የትምህርት ጥራትን በማሻሻል የህብረተሰቡን ችግር በቴክኖሎጂ በመታገዝ የሚፈታ ትውልድ ለመፍጠር የተለያዩ ተግባራትን ሲሰራ መቆየቱን የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

“ትምህርት ለሰው ሃብት ልማት” በሚል መርህ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀው እና ለትምህርት ሥርዓቱ ወሳኝ መሆኑ የተገለጸ የትምህርት ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

እንደ ኦሮሚያ 2.4 ሚሊዮን ተማሪዎች የትምህርት ዕድል አግኝተዋል ያሉት የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር)፤ በ2017 የ12ኛ ክፍል ፈተና 900 ተማሪዎች ከ5 መቶ በላይ ውጤት በማምጣት ወደ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት አምጥተዋል ብለዋል።

ትምህርት ከአካባቢና ተፈጥሮ ጋር የሚዛመድ የቴክኖሎጂ ዕውቀት ያለው ትውልድ ለመፍጠር ወሳኝ አቅም የሚፈጥር ነው ያሉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ፤ መንግስት እንደሀገር የትምህረት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሻሻል እና የነገ መሠረት የሆነውን ትውልድ ለመፍጠር ሰፋፊ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።

ከእነዚህም መካካል በትምህርት ለትውልድ መርሃ ግብር በርካታ ትምህርት ቤቶች ምቹ እንዲሆኑና የግብዓት አቅርቦት እንዲኖራቸው መሠራቱንም ተናግረዋል።

በዚህ ጥረትም በሀገር አቀፍ ደረጃ የኦሮሚያ ክልል በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የተሻለ ውጤት ማስመዝገቡንም አመላክተዋል።

በመርሐ- ግብሩም ለ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የላቀ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ዕውቅና እና ሽልማት ይሰጣል።

በአለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review