በመዲናዋ የተከናወኑ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች ለህግ ማስከበር ስራ የላቀ አበርክቶ እያደረጉ መሆኑ ተገለፀ

You are currently viewing በመዲናዋ የተከናወኑ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች ለህግ ማስከበር ስራ የላቀ አበርክቶ እያደረጉ መሆኑ ተገለፀ

AMN – ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም

‎በመዲናዋ የተከናወኑ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች ለህግ ማስከበር ስራ የላቀ አበርክቶ እያደረጉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ገለጹ።

‎ይህንን የገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ኮሚሽን ሰራዊት አባላትም በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በጎበኙበት ወቅት ነው ።

በጉብኝት ‎መርሐ ግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋዉ እንደተናገሩት፣ የልማት ስራዎቹ የህዝቡን ተጠቃሚነትና የከተማዋን ሁሉንተናዊ እድገት ከማጉላት ባሻገር የህግ ማስከበር ስራን በእጅጉ ያገዙ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።

‎የተሰሩ ስራዎችን የመጠበቅና በቀጣይም የሚከናወኑ ስራዎችን ስኬታማነታቸውን ለማረጋገጥ እንደ ተቋም ድርብ ኃላፊነት እንደሚወስዱም ነው ኮሚሽነር ጌቱ የተናገሩት።

‎የፖሊስ ሰራዊት አባላቱ በበኩላቸው፣ የተከናወኑ ስራዎች የከተማዋን ውበት ከማጉላት ባለፈ ሰዉ ተኮር እና ለምጣኔ ኃብታዊ እድገትም የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ገልጸዋል።

‎ለፕሮጀክቶቹ ስኬታማነት የራሳችንን አስተዋጽኦ አበርክተናል ያሉት አባላቱ በዚህም ልባዊ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።

‎በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review