የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2018 የውድድር ዓመት ዛሬ ይጀመራል

You are currently viewing የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2018 የውድድር ዓመት ዛሬ ይጀመራል

AMN – ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2018 የውድድር ዓመቱን ዛሬ በይፋ ይጀምራል።

20 ክለቦችን የሚያሳትፈው የዘንድሮው ውድድር በሁለት ምድብ ተከፍሎ ይከናወናል።

አዲስ አበባ እና ሃዋሳ ውድድሩ የሚጀመርባቸው ከተሞች ናቸው።

በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያዎቹን ዘጠኝ ሳምንታት ሃዋሳ ደግሞ አምስት ሳምንታትን ያስተናግዳሉ።

ሊጉ ነገ ሲጀመር በአዲስ አበባ ስታዲየም 7 ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማን ይገጥማል።

9 ሰዓት ላይ ሌላው ከከፍተኛ ሊግ ያደገው አርሲ ነጌሌ ከአርባምንጭ ከተማ ይጫወታል።

በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከ ሲዳማ ቡና 9 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ይጀምራሉ።

ድሬዳዋ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ምሽት 12 ላይ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review