የከተማዋን የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ መጀመሩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

You are currently viewing የከተማዋን የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ መጀመሩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

AMN – ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ ዛሬ ማለዳ የከተማችንን የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል ብለዋል።

በግምገማ መድረኩ በሩብ ዓመቱ የታቀዱ እና የ90 ቀን አበይት ተግባራት የደረሱበት የአፈፃፀም ደረጃ እንደሚገመገም ገልፀዋል፡፡

መድረኩ የተገኙ ዉጤታማ አፈፃፀሞችን ይበልጡን አልቀን በማስቀጠል እና የታዩ ጉድለቶችን በማረም እንዲሁም ትኩረት እና የተለየ ርብርብ የሚሹ ተግባራትንም ለይተን ቀጣይ አቅጣጫ የምናስቀምጥበት ይሆናል ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review