በሩብ አመቱ ከተከናወኑ ቁልፍ ተግባራት መካከል የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ቦሌ ቅርንጫፍ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ እንደሚገኝበት ተመላከተ

You are currently viewing በሩብ አመቱ ከተከናወኑ ቁልፍ ተግባራት መካከል የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ቦሌ ቅርንጫፍ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ እንደሚገኝበት ተመላከተ

AMN – ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ካከናወናቸው ቁልፍ ተግባራት መካከል የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ቦሌ ቅርንጫፍ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ እንደሚገኝበት ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ መካሄድ ቀጥሏል ።

በሩብ ዓመት ሪፖርቱ ከተካተቱ ቁልፍ ተግባራት መካከል መንግስታዊ አገልግሎትን ዲጂታላይዝ ፣ ቀልጣፋ፣ አስተማማኝ፣ ተደራሽና ፍትሃዊ በማድረግ የተገልጋይን ወጪና ጊዜ ለመቀነስ በሩብ አመቱ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ቦሌ ቅርንጫፍ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ለአብነት ተመላክቷል።

በማዕከሉ ውስጥ 13 የማዕከል ተቋማት ፣ 3 የፌደራል እና 2 የፋይናንስ ተቋማት ተሳታፊ ሲሆኑ በማዕከል [107] እና በቦሌ ቅርንጫፍ [96 ] አገልግሎቶች ተለይተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆኑ 157 የአገልግሎት ካውንተሮች በማዕከል (101) እና በቦሌ ቅርንጫፍ (56) መዘጋጀታቸውም መመላከቱም ከከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review