አሁን ያለዉ የጥቅምትና ቀጣይ ወራት ነፍሻማና ደረቅ የአየር ንብረት ለእሳት መከሰትና መባባስ አስተዋጾው ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰብ እሳትና የእሳት ምንጮችን በሚጠቀም ጊዜ ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል ።
ያለፉት ተመሳሳይ ጊዚያት መረጃዎች እንዲሚያመለክቱት ከጥቅምት ወር ጀምሮ ባሉ ተከታታይ ወራት ከሌሎች ወራት በተለየ የእሳት አደጋ ያጋጠመበትና ከፍተኛ ውድመት የስከተለበት ወር ነው ::
መላው የከተማ ነዋሪና የንግድ ማዕከላት እንዲሁም የማምርቻ ተቋማት እሳትና የኤሌክትሪክ ኃይል ፣ ከእሳት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ግብአቶች ሲጠቀም ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግና በተለያዩ አማራጮች ከኮሚሽኑ የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በመተግበር እራሱን ንብረቱን ከአደጋ እንዲጠብቅ መልዕክት ተላልፏል፡
በሌላ በኩል ከዚህ አልፎ ለማያጋጥሙ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት የተደረገ በመሆኑ አደጋ በአጋጠመ ጊዜ በነጻ የስልክ መስመር በ939 ፈጥኖ ማሳወቅ እንደሚገባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡